ህወሓት ህዝባዊ ኮንፈረንስ ማካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ በመቐለ ከተማ ህዝባዊ ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው።
በኮንፈረንሱ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ፥ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ነባር ታጋዮችና የሃይማኖት መሪዎች፣ የህዝብ ተወካዮችና የሲቪክ ማህበራት እየተሳተፉ ይገኛል።
ከዚህ ባለፈም የሴቶች ተወካዮች፣ ምሁራን፣ ወጣቶች እንዲሁም የኢሮብና ኩናማ ብሄረሰብ ተወካዮችም ተገኝተዋል።
ኮንፈረንሱ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፥ በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሚመክር ይሆናል።