የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት ለ2013 ዓ.ም 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ሲያፀድቅ አዲስ ከንቲባም ሾሟል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አድርጎ የሾመው የከተማዋ ምክር ቤት የከተማዋን በጀት 2 ቢሊየን 54 ሚሊየን 18 ሺህ ብር ብር አድርጎ አፅድቋል።
የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።
ምክር ቤቱ በሲዳማ ክልል ብልፅግና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሀም ማርሻሎ አቅራቢነት ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን በምክትል ከንቲባ ማዕረግን ሹመት ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በቀድሞው ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የአሁኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ሀላፊ ሆነው የተሾሙትን የቀድሞውን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የሚተኩ ይሆናል።