Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኤልያስ ሽኩር ከዓለም አቀፉ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር ከዓለም አቀፉ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ፕሬዚዳንት ዊቶልድ ባንካ ጋር በቪድዮ ኮንፈረንስ ውይይት አካሂደዋል ።

አቶ ኤሊያስ በውይይታቸው እንዳሉት ፀረ አበረታች ቅመሞች ስፖርቱን ከመጉዳት ባሻገር የሰው ልጅ የጤና ጠንቅ እየሆኑ መምጣታቸውን ተናግረዋል።

በመሆኑም የስፖርት አበረታች ቅመሞችን በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የስፖርት ቤተሰቡን ግንዛቤ የማስጨበጥ፣ ህጎችን ተግባራዊ የማድረግ ስራ በከፍተኛ ትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል ።

ፀረ አበረታች ቅመሞችን በመከላከል ስፖርትን በማስፋፋት ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ያላትን ዝና እና ክብር አስጠብቃ እንድትቀጥል እየተሰራ መሆኑንም ለፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል ፡፡

ኮሚሸነሩ አያይዘውም ኢትዮጵያ በፀረ አበረታች ቅመሞች ላይ የጀመረችውን እንቅስቃሴ በማጠናከር በቀጣይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ የሚደረገውን የዓለም አቀፉ የፀረ- አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ተግባራዊ በማድረግ ከአፍሪካ ቀዳሚ እንድትሆን ጥረት ይደረጋል ብለዋል።

የዓለም አቀፉ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ፕሬዚዳንት ዊቶልድ ባንካ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ አድንቀው የተሰሩ ስራዎች ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ እንደሚሆኑ ጠቅሰዋል፡፡

በመሆኑም የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ እና የዓለም አቀፉ የፀረ-አበረታች መድሃኒት ኤጀንሲ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ማስታወቃቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.