የማህፀን ጫፍ ካንሰር የቅድመ ምርመራና ጠቀሜታው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የካንሰር ቅድመ ምርመራ የካንሰር ህመም ከመከሰቱ እና ጉዳት ሳያመጣ በፊት ህክምና በማድረግ በሽታውን መከላከል ማለት ነው።
የማህፀን ጫፍ ካንሰር የቅድመ ምርመራ አስፈላጊነት…
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ሆስፒታል ለህክምና መጥተው ሲመረመሩ ከ7 ሺህ በላይ ሴቶች የማህፀን ጫፍ ካንሰር ተጋልጠው የተገኙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑት በዛው ዓመት ህይወታቸው እንደሚያልፍ የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዶካክ ኮሌጅ መረጃ ያመለክታል።
ይህ አሃዝም የሚያመለክተው ህመም ኖሯቸው ለመታከም ወደ ህክምና ማእከል የሄዱትን ሴቶች ብቻ እንደሆነ ነው መረጃው የሚያመለክተው።
የማህፀን ጫፍ ካንሰር የቅድመ ምርመራን ማን ማድረግ አለበት…?
- እድሜዋ ከ21 ዓመት በላይ የሆነና ጾታዊ ግንኙነት የጀመረች ሴት
- ከዚህ በፊት ተመረምራ ነፃ ከተባለች 3 ዓመት ያለፋት
- የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያዳክሙ መድኃኒቶችን የምትወስድ ወይም የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቫይረስ በደሟ ውስጥ ያለ።
የማህፀን ጫፍ ካንሰር የቅድመ ምርመራ ምን ይጠቅማል…?
- ካንሰር አለመኖሩን ማረጋገጥ
- የቅድመ ካንሰር ምልክቶች ካሉ ባግባቡ ለመታከም
- የተረጋገጠ ካንሰር ከተገኘ በወቅቱ ህክምናውን በመውሰድ ለመዳን
- ውጤትን አውቆ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ለማድረግ