የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምስት ተጫዋቾች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምስት ተጫዋቾች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
ፌዴሬሽኑ ካሜሩን ለምታዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት 40 ተጫዎች መጥራቱ ይታወሳል፡፡
ጥሪ ተደርጎላቸው ከተገኙ 36 ተጫዎቾች ውስጥም አምስቱ ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል ብሏል፡፡
ቀሪዎቹ የቡድኑ አባላት ካፍ አካዳሚ ትናንት መግባታቸው ነው የተነገረው፡፡
ፌዴሬሽኑ ለእያንዳንዱ ተጫዋች የግል ህይወት ነጻነት ሲባል እና በስነ ልቦናም እንዳይጎዱ የተጫዋቾቹን ስም ይፋ አላደረገም፡፡
ከ72 ሰዓታት በኋላ ቫይረሱ ያልተገኘባቸው ተጫዋቾች እና የቡድኑ አባላት በሙሉ ምርመራ የሚደረግላቸው ይሆናል።
ቡድኑን ዘግይተው የተቀላቀሉት ተከላካዩ አንተነህ ተስፋዬ እና ሱራፌል ዳኛቸው እንዲሁም የቡድኑ ወጌሻ በነገው እለት የኮቪድ ምርመራ የሚደረግላቸው ይሆናል።