612 ተጨማሪ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው 390 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ4 ሺህ 747 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 612 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡
አሁን ላይም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 73 ሺህ 944 ደርሷል።
ሚኒስትሯ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት 390 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውንም አስታውቀዋል፡፡
ይህን ተከትሎም እስካሁን 30 ሺህ 753 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም 7 ሰዎች በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሲሆን እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 1 ሺህ 177 ደርሷል፡፡
አሁን ላይ 42 ሺህ 12 ሰዎች ቫይረሱ ያለባቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 247 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ ናቸው ተብሏል፡፡