በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 738 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 10 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 8 ሺህ 355 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 738 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 66 ሺህ 224 ደርሷል።
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የ10 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር 1 ሺህ 45 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መረጃ ያመለክታል።
በ24 ሰዓታት ውስጥ 677 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ስሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 26 ሺህ 665 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
38 ሺህ 512 ሰዎች በአሁን ወቅት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሲሆን 270 ፅኑ ህሙማን ደግሞ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል።