ፌስቡክ በጓደኞች ጥቆማ ሂደት ላይ ስልክ ቁጥሮችን መጠቀም ሊያቆም ነው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣2012 (ኤፍቢሲ) ፌስቡክ ከግል መረጃ መጠበቅ ጋር ተያይዞ የአባላት የስልክ ቁጥሮች በጓደኞች ጥቆማ ሂደት ላይ መጠቀም ሊያቆም መሆኑ ተገለፀ ፡፡
የተጠቃሚዎች የፌስቡክ አድራሻ በጠላፊዎች በቀላሉ እንዳይገኝ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ኮድ እንዲላክ ምርጫ ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ሆኖም ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን ስልክ ቁጥር ለማስታወቂያ እና በጓደኛ ጥቆማ ሂደት ላይ ሲጠቀምበት እንደነበረ አስታውቋል፡፡
በአሁን ወቅት ከአሜሪካ አዲስ የቁጥጥር ስርዓት ጋር ተያይዞ ይሄን አሰራር ለማቆም ዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡
ምንጭ፣ ቢቢሲ