በኢትዮጵያ በዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ዙሪያ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ
አዲስ አበባ ፣ጳጉሜን 3 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድና የ2013የበጀት አመት የእቅድ ትስስርላይ ውይይት አካሄደ፡፡
በውይይቱ በኢትዮጵያ የተፈጥሮ እና የዱር እንስሳት ሃብት ስፋትና ስብጥሩ በዓለም ደረጃ ወደር የማይገኝለት ቢሆንም በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዳልዋለ የተገለፀ ሲሆን ይህን የተፈጥሮ ፀጋ በአግባቡ በመጠበቅ በመንከባከብና በማልማት ሀገራዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ማሳደግ እንደሚገባ ተገልጿል።
ዱር እንስሳት የተፈጥሮ ጸጋ በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ሁኔታ ላይ የማይገኝ በመሆኑ ለውጥ ማምጣት በሚያስችል ሁኔታ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በተቀናጀ ሁኔታ መስራት አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም አስገዳጅ ሆኖ በመገኘቱ ይህን የአሥር ዓመት የብልጽግና ልማት ዕቅዱ መዘጋጀቱ የተገለፀ ሲሆን መተማመንና የእቅድ ትስስር ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ተነግሯል፡፡
በውይይቱ የ2012 የበጀት ዓመት አፈፃፀም ላይ የተመከረ ሲሆን በዚህም የኮሮና ወረርሽኝ ከፈጠረው ጫና አንፃር የዓመታዊ በጀት አጠቃቀም በመደበኛ 96 በመቶ እንዲሁም በካፒታል በጀት 78 በመቶ መሆኑ ተገልጿል፡፡
አፈፃፀሙ የተሻለ እንደሆነ እና የታዩ ክፍተቶችን ፤ በተለያዩ ምክንያቶች ያልተፈፀሙ ተግባራት በሚቀጥለው አሥር ዓመት መሪ እቅድ ውስጥ እንደሚካተት ከኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።