ኢትዮጵያ ዛሬ ያመጠቀችው ሳተላይት በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃትና መነሳሳትን የሚፈጠር ነው- ወ/ሮ ያለም ፀጋይ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ዛሬ ያመጠቀችው ሳተላይት በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃትና መነሳሳትን የሚፈጠር መሆኑን የኢፌዴሪ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ገለፁ።
ሚኒስትሯ ወይዘሮ ያለም ፀጋይ የዩዝ ኮኔክት ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ሲጀመር ነው ይህን ያሉት።
በዚሁ ወቅት ሚኒስትሯ ወጣቶች ለሀገራቸው ሰላምና ልማት ሊሰሩ ይግባል ብለዋል።
መንግስትም የወጣቶችን የስራ አጥነት ችግር ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝም ነው ያነሱት።
የግሉ ዘርፍ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትም መንግስት የወጣቶችን ጥያቄ ለመመለስ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
ዩዝ ኮኔክት ፕሮግራም የአፍሪካ ወጣቶችን ትስስር ለማጠናከር በአውሮፓውያኑ 2012 በሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሚ የተጀመረ ነው።
ዮዝ ኮኔክት በኢትዮጵያ ሲጀመር ትኩረት ያደረግነው በአምስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሯ፥ የሀገሪቱ ወጣቶችን በሰላምና ዴሞክራሲ ግንባታ ሚናቸውን ለማሳደገግ፣ ምቹ የስራ እድል ፈጠራን ለማሳደግ፣ ወጣቶች ዓመቱን ሙሉ በበጎ ፈቃድ ስራ እንዲሰማሩ ለማድረግ፣ ወጣቶችን ለአመራር ለማብቃትና የስርዓተፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ መሆኑን ጠቁመዋል።
“የወጣቶች ትስስር ለምክንያት” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ፕሮግራም ወጣቶች፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ አምባሳደሮች እና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።