Fana: At a Speed of Life!

በ500 ሚሊየን ብር በአዳማ ከተማ የተገነባው ሀይሌ ሪዞርት ዛሬ ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 28 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሀይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ድርጅት በ500 ሚሊየን ብር በአዳማ ከተማ ያስገነባው 7ኛው የሀይሌ ሪዞርት ዛሬ ተመርቋል።

በሪዞርቱ የምርቃት ስነስርዓት ላይ ሻለቃ ሀይሌን ጨምሮ የሪዞርቱ የስራ ሃላፊዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

ዛሬ የተመረቀው ሪዞርት ሰፋፊና ምቹ የመመገቢያና የስብሰባ አዳራሾች ጨምሮ 106 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች፣ የስፖርት ማዘወትሪያ ስፍራዎች፣ የመዋኛ ገንዳዎች እና ሌሎችንም መሰረተ ልማቶችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

በአዳማ የተገነባው ሰባተኛው ሪዞርት በ 500 ሚሊየን ወይም በግማሽ ቢሊየን ብር ወጪ ተገነባ መሆኑን ሀይሌ በመግለጫው ገልጿል።

ከዚያም ባለፈ 300 ለሚሆኑ ዜጎችም የስራ እድል መፍጠሩን ተናግሯል።

ሪዞርቱ በግንባታም ሆነ በአገልግሎቱ ከሌሎች ሪዞርቶች ለየት ባለ መልኩ መቅረቡን የተናገረው ሻለቃ ሀይሌ÷ ከባለ 4 እና 5 ኮኮብ ደረጃን የሚያሟሉ አገልግሎቶችን እንደሚሠጥ ገልጿል።

ግንባታውንም ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመታትን የፈጀ ሲሆን በአዲሱ ዓመት እየተገነቡ ያሉ ሶስት ሪዞርቶችእንደሚጠናቀቁ ገልጿል

በፍሬህይወት ሰፊው

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.