ለ6 ዓመታት ግንባሩን ብቻ ፎቶ በማንሳት አንድ የትስስር ገፅ ላይ የለጠፈው ሰው
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለ6 ዓመታት ግንባሩን ብቻ ፎቶ በማንሳት አንድ የትስስር ገፅ ላይ የለጠፈው ሰው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።
የ25 ዓመቱ ግሪካዊ ለ6 ዓመታት ግንባሩን ምስል ብቻ በኢንስትግራም ገፁ ላይ በመለጠፍ ወይም ፖስት በማድረግ መነጋገሪያ መሆን ችሏል።
ይህን ማድረግ የጀመረውም ከስድስት ዓመት በፊት መሆኑ የተነገረለት ግለሰቡ ለሴት ጓደኛው እንደ ጨዋታ የግንባሩ ምስል ብቻ መላክ እንደጀመረ እና ከዚያም በትስስር ገፁ ላይም መለጠፍ መጀመሩን ተናግሯል።
ይህን ልማድም አስር ዓመት እስኪያስቆጥር የማቆም ፍላጎት እንደሌለው ተናግሯል።
እንደ ኦዲቲ ሴንተራል መረጃም ግለሰቡ ኢንስተግራም ተከታዮቹምይህን ድርጊቱን እንደሚወዱት ተናግሯል።
ግለሰቡ ትስስር ገፁን የሚጠቀመው ለዚህ አላማ ብቻ ሲሆን፥ በቋሚነት በሳምንት ቢያንስ አንዴ ግንባሩን ብቻ ፎቶ በማንሳት ይለጥፋል።