Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ26 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 26 ሚሊየን አለፈ።

ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ እስከ አሁን ድረስ 26 ሚሊየን 37 ሺህ 404 ሰዎች መያዛቸውን ይፋ አድርጓል።

ተቋሙ በድረ ገጹ እንዳሰፈረው ሦስት አገራት እያንዳንዳቸው ከ3 ሚሊየን በላይ ዜጎቻቸው በወረርሽኙ ተይዘዋል።

አሜሪካ ከ79 ሚሊየን በላይ ዜጎቿን መርምራ ከ6 ሚሊየን በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

እንዲሁም ብራዚል እና ህንድ ወደ 4 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎቻቸው በቫይረሱ መያዛቸ ተነግሯል፡፡

እስከ አሁን በወረርሽኙ ከተያዙት ከ26 ሚሊየን በላይ ከሚሆኑት ሰዎች ውስጥ 863 ሺህ 119 ያህሉ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እስከ አሁን ድረስ ከ 17 ሚሊየን በላይ ሰዎች ማገገማቸውን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በአፍሪካ አህጉር ደቡብ አፍሪካ ትልቁን ቁጥር በመያዝ 630 ሺህ 595 ዜጎቹ ተይዘዋል፡፡

እንዲሁም ከ6 መቶ ሺህ ዜጎች ውስጥ 14 ሺህ 389 የሚሆኑት ህይወታቸውን ሲያጡ 553 ሺህ 456 ሰዎች አገግመዋል፡፡

ግብጽ 99 ሺህ 280፣ ሞሮኮ 65 ሺህ 453፣ ናይጄሪያ 54 ሺህ 463 የሚሆኑ ዜጎቻቸው በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

በኢትዮጵያም እስከ ትናንት ድረስ አጠቃላይ ለ949 ሺህ 813 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 54 ሺህ 404 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው፤ 19 ሺህ 903 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

 

#FBC የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.