Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለኮሮና ቫይረስ ክትባት ለማግኘት በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት አልሳተፍም አለች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለማግኘት እና ምርቱን ለማሰራጨት በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ላይ አልሳተፍም ማለቷ ተሰምቷል፡፡

በዓለም አቀፍ ጥረቱ ላይ በዓለም ጤና ድርጅት በኩል ከ150 ሃገራት በላይ ቅንጅት ፈጥረው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ይህ ኮቫክስ የተሰኘው ጥረት ሀገራት ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ ክትባት ለማግኘት ይረዳቸዋል ነው የተባለው፡፡

ሆኖም የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በበኩሉ ክትባቱን ለማግኘት ሀገራቸው ብቻዋን እንደምትቆም ነው የገለጸው፡፡

ትራምፕ በግንቦት መጨረሻ ዋሽንግተን ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር ያላትን ግንኙነት እንዳቋረጠች ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በወቅቱ ቻይና ድርጅቱ ላይ ጫና እያሳረፈችና እየተቆጣጠረችው ነው ሲሉም ወቅሰዋል።

አስተዳደሩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር ባለው ግንኙነት የተነሳ ነው ተብሏል፡፡

እስከ አሁን ድረስ አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለማግኘት ሦስተኛ ደረጃ ሙከራ ላይ ናቸው፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ለብቻዋ በምታደርገው ጥረት ክትባቱ ከመጪው ምርጫ ቀደም ብሎ ይፋ እንደምታደርግ ተናግረዋል፡፡

እስከ አሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 26 ሚሊየን እየተጠጋ ይገኛል፡፡

ከ18 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ማገገማቸውን ከዓለም ጤና ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.