ጉግል የክሮም 79 አዲስ ማዘመኛን አስወገደ
ኩባንያው ከተጠቃሚዎች የቀረበውን ቅሬታ ተከትሎ ባደረገው ፍተሻ አዲሱ ማዘመኛ ላይ በርካታ ክፍተት ማግኘቱን ገልጿል።
ተጠቃሚዎቹም በሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች ማዘመኛውን ለመጠቀም በሚሞክሩበት ጊዜ እንደሚጠፋባቸው ተናግረዋል።
ይህ ችግር አንድሮይድ ስልኮችን በሚጠቀሙ ደንበኞች ላይ የተከሰተ ሲሆን፥ የተፈጠረውን ክፍተት ለማስተካከልም የሳምንት ጊዜ ያስፈልገኛል ብሏል ጉግል።
እስከዛው ድረስ ግን አዲሱን ማዘመኛ ለጊዜውም ቢሆን ማስወገዱን ነው የገለጸው።
አዲሱ የክሮም 79 ማዘመኛ ዓለም ላይ 50 በመቶ ለሚሆኑ የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች መለቀቁ ነው የተነገረው።
የማሻሻያ ሂደቱን ተከትሎ ምንም አይነት መረጃ እንደማይጠፈ የተገለፀ ሲሆን መረጃው የሚቀመጥበት ቦታ ለውጥ ይካሄዳል ተብሏል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ