የአማራ ክልል የካቢኔ አባላት ለገበታ ለሐገር ፕሮጀክት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ወሰኑ
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል የካቢኔ አባላት ለገበታ ለሐገር ፕሮጀክት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ወሰኑ፡፡
የካቢኔ አባላቱን ውሳኔ ይፋ ያደረጉት የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ናቸው፡፡
በገበታ ለሐገር ፕሮጀክት በአማራ፣ ደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ የጎብኚ መዳረሻዎችን ለማልማት የታቀደ ሲሆን 3 ቢሊየን ብር ለማሰባሰብ መታቀዱም ይታወሳል።
በአማራ ክልል ጎርጎራ ላይ የታሰበው ፕሮጀክት የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃትና ገጽታን ለመገንባት ጉልህ ድርሻ ይኖረዋልም ብለዋል።
በተጨማሪም ለፕሮጀክቱ ዕውን መሆን መላውን ሕዝብ የሚያሳትፍ የገቢ ማሰባሰብ መርሐ ግብር እንደሚዘጋጅም ተናግረዋል።
በተያያዘ ዜና የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች ለገበታ ለሐገር ፕሮጀክት የአንድ ወር ደመወዛቸውን መስጠታቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ በትዊተር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል፡፡