የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በ2024 ስልጣን ሊለቁ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጡ
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 8፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በፈረንጆቹ 2024 ላይ ስልጣን ሊለቁ እንደሚችሉ ተናገግረዋል።
ፕሬዚዳንቱ በ2024 የሚያልቀውን የስልጣን ዘመናቸውን ከጨረሱ በኋላ በ4ኛ ሀገር አቀፍ ምርጫ የመወዳደር ፍላጎት እንደሌላቸው በዶሃው መድረክ ላይ ተናግረዋል፡፡
የቀድሞው የአማጺያን ቡድን መሪ ፓል ካጋሜ ፥የ1994ቱን የሩዋንዳንየዘር ጭፍጨፋ በማስቆም ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸው ይነገራል።
ከፈረንጆቹ 2000 ጀምሮ በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ በ2017 የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተከትሎ የሀገሪቱን የምርጫ ጊዜ ለሁለት ሰባት ዓመታት ማራዘማቸው ይታወሳል።
የ62 ዓመቱ ካጋሜ በቅርቡ ቡና አምራች ሀገር የሆነችው ሩዋንዳን ለማረጋጋትና ኢኮኖሚዋን ለመለወጥ ባደረጉት ጥረት ዓለም አቀፍ አድናቆትን አግኝተዋል፡፡
ሩዋንዳ ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት ከሚያድጉ የአፍሪካ ሀገሮች ውስጥ አንዷ ስትሆን በዚህ ዓመት 8 ነጥብ 5 በመቶ እድገት እንደምታስመዘግብ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡-ሲ.ጂ.ቲ.ኤን