በአማራ ክልል በመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚሰሩ የአዴፓ አባላት በብልፅግና ፓርቲ ዙሪያ ውይይት እያካሄዱ ነው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል በመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚሰሩ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አባላት በብልፅግና ፓርቲ ዙሪያ ከክልሉ ከፍተኛ ስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡
አባላቱ በብልፅግና ፓርቲ አስፈላጊነት ፣ ፕሮግራም ፣ ህገ ደንብ ዙሪያ ነው ከስራ ሃላፊዎቹ ጋር እየመከሩ የሚገኙት፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች የብልፅግና ፓርቲ ስራ አጥነትን እና የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ ፣ ሀገራዊ መግባባትን ከመፍጠር አኳያ እንዲሁም የፓርቲው ህገ ደንብ ከኢህአዴግ ህገ ደንብ የሚለይበት ነጥቦች ምንድ ናቸው የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡
ለጥያቄዎቹም አማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው እና ሌሎች የፓርቲው የስራ ሃላፊዎች ምላሽ እየሰጡበት ይገኛል፡፡
በዙፋን ካሳሁንና ናትናኤል ጥጋቡ