የፊቼ ጫምባላላ በዓል የሰላም፣ የአንድነትና የአብሮነት በዓል ነው – ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፊቼ ጫምባላላ በዓል የሰላም፣ የአንድነትና የአብሮነት በዓል ነው ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።
የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል ዋዜማ “ፊጣሪ ሃዋሮ” በመባል የሚታወቀው ክብረ በዓል የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ፋንታዬ ከበደን ጨምሮ የክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ የስራ በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።
ርዕሰ መስተዳድር ደስታ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት÷ የፊቼ ጫምባላላ በዓል ሰላም፣ አብሮነትና ፍቅር የበዛበት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተመዘገበ የዓለም ቅርስ እንደሆነ ገልጸዋል።
እሴቱን ጠብቀው ያቆዩ አባቶች ያላቸው እውቀት የሚደነቅ መሆኑንም አውስተዋል።
የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የአብሮነት የፍቅር በዓል ይሁንልን ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በብርሃኑ በጋሻው