Fana: At a Speed of Life!

ፍቼ ጫምባላላ የአብሮነት እና የህብረ ብሔራዊነት ነፀብራቅ የሆነ ድንቅ በዓል ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ለፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አቶ አደም ፋራህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የድንቅ ባህል ባለቤት የሆነው ታላቁ የሲዳማ ህዝብ በራሱ የጊዜ ቀመር ላይ ተንተርሶ የሚያከብረው ይህ በዓል ዘመንን ከመለወጥ ባሻገር ተስፋን፣ መታደስንና ብሩህነትን የሚሰንቅበት የአዲስ ዘመን ብስራት የብሩህ ቀን ወጋገን ነው ብለዋል።

ምስጋና፣ ፍቅር፣ አንድነት፣ እርቅ፣ ሰላም፣ በጎነት የፍቼ ጫምባላላ በዓል ፍሬዎች መሆናቸውንም ገልጸዋል።

እጅግ ልዩ ስፍራ በሚቸረው በዓል ላይ የተጣላው የሚታረቅበት፣ የተለያየው የሚገናኝበት፣ የአብሮነት እና የህብረ ብሔራዊነት ነፀብራቅ የሆነ ድንቅ በዓል እንደሆነም አመላክተዋል።

እንደ ብልፅግና ፓርቲ በቀጣይ በዓሉ ከዚህ በላቀ ሁኔታ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ብሎም የበዓሉ ትሩፋቶች ለሀገራዊ አንድነት እና ለህብረ ብሔራዊነት ተጨማሪ አቅም እንዲሆን አበክረን መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.