ሚኒስቴሩ ለዲፕሎማቲክ ማኀበረሰቡ የኢፍጣር መርሐ- ግብር አካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይሚኒስቴር መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማኀበረሰብ የኢፍጣር መርሐ- ግብር አካሄደ፡፡
የኢፍጣር መርሐ- ግብሩ የተካሄደው በስካይላይት ሆቴል መሆኑን ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ትስሥሥር ገጹ አስታውቋል፡፡
በመርሐ-ግብሩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስን (ዶ/ር) ጨምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሃጂ ሼኽ ኢብራሂም ቱፋ እንዲሁም ተጋባዥ የዲፕሎማቲክ ማኀበረሰብ ክፍሎች መሳተፋቸው ተመላክቷል፡፡