Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል- አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች ጋር በሰላምና ፀጥታ ላይ ያደረጉት ምክክር የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በመድረኩ ማጠቃለያ እንደገለፁት፤ ኢተገማች በሆነው የዓለም ሁኔታ ክልላዊ፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታን ፈጥኖ በመረዳት ሁሌም ቀድሞ ለመገኘት ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል።

የክልሉ መንግሥት ለሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት ባከናወናቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎች በክልሉ አንጻራዊ ሰላምና የተረጋጋ የፀጥታ ሁኔታን ማስፈን ተችሏል ብለዋል፡፡

ይህም ክልሉ ከመደበኛ የልማት ስራዎች ባሻገር ትልልቅ ሀገራዊ ኩነቶችን በስኬት በማስተናገድ በሰላም ማጠናቀቅ አስችሎታል ማለታቸውን የርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት በቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

በሰላም ረገድ የተመዘገበው ስኬት የክልሉን የኢንቨስትመንት ፍሰትና የቱሪዝም ዘርፍ በከፍተኛ ሁኔታ በማነቃቃት ለፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ለዘላቂ ልማት ምቹ መደላድል መፍጠሩን ገልፀዋል፡፡

የፖሊስ መኮንኖች ነፃና ገለልተኛ ሆነው ሙያዊ ስነ ምግባር በመላበስ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት ህብረተሰቡን በቅንነት ማገልገል እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይም ጊዜያዊና ወቅታዊ ፈተናዎችን በብቃት መሻገር የሚችል የፖሊስ ሰራዊት እና የማይበገር ተቋም ለመገንባት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.