Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የከተማ ልማት ስኬታማ ተሞክሮዋን በዩኤን ሃቢታት ስብሰባ ላይ አካፈለች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የከተማ ልማት ስኬታማ ተሞክሮዋን በናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው የዩኤን ሃቢታት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ስብሰባ ላይ አካፈለች፡፡

በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ፈንታ ደጀን የተመራ ልዑክ በስብሰባው ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

ዩኤን ሃቢታት በኢትዮጵያ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በተመለከተ ሪፖርት በስብሰባው ላይ የቀረበ ሲሆን፥ የኢትዮጵያ የከተማ ልማት ሥራ አድናቆት እንደተቸረው ተገልጿል።

በዩኤን ሃቢታት ድጋፍ እየተተገበሩ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች ከኢትዮጵያ የከተማ ልማት ፖሊሲና ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ሚኒስትር ዴዔታው አንስተዋል።

የዜጎችን ሕይዎት ለማሻሻል እየተተገበሩ ለሚገኙ ኢኒሼቲቮችና ለመሠረተ ልማት ሥራዎች፤ ድርጅቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ ማቅረባቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.