ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው 9 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ እንዲገቡ ተወሰነ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መሥተዳድር ምክር ቤት ባካሄደው 38ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
በዚሁ መሠረት ምክር ቤቱ በግብርና፣ ኢንዱስትሪና አገልግሎት የስራ ዘርፎች ለመሰማራት ከ527 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል በማስመዝገብ የቀረቡ ዘጠኝ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎችን መርምሮ ወደ ስራ እንዲገቡ ወስኗል።
እንዲሁም በምርጥ ዘር ድርጅት፣ በማሕበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን እና በኮሪደር ልማት ዙሪያ መወያየቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡