Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ በያዝነው ዓመት ከ36 ሺህ ሔክታር መሬት በላይ በተፋሰስ ልማት ማልማት ተቻለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በያዝነው ዓመት 22 ሚሊየን ሰዎችን በማሳተፍ 36 ሺህ 400 ሔክታር መሬት በተፋሰስ ልማት ማልማት መቻሉን የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ መምሩ ሞኬ ገለጹ፡፡

ዘንድሮ ለተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በላቀ የሕዝብ ንቅናቄ መሥራት መቻሉንም ነው ኃላፊው የገለጹት፡፡

በዚህም በክልሉ የተሠሩ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራዎች ለምርትና ምርታማነት እድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ አበርክተዋል ማለታቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

በተከናወኑ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች በለሙ ቦታዎችም አርሶአደሮች የተለያዩ የእንስሳት መኖዎችና ሌሎች የሰብል አይነቶችን እንደሚያለሙ ጠቁመዋል፡፡

ጎን ለጎንም ለእርሻ ሥራ ምቹ ባልሆኑ ቦታዎች ላይ የቀርከሃ ልማት ሥራ እንሚያከናውኑ አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.