Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በ10ኛው የብሪክስ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እቅድ ውይይት ላይ ተሳተፈች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በብራዚል እየተካሄደ በሚገኘው 10ኛው የብሪክስ ውጭ ጉዳይ ፖሊስ እቅድ ውይይት ላይ ተሳትፋለች፡፡

በመድረኩ ኢትዮጵያን ጨምሮ የብሪክስ አባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

በውይይቱ የአባል ሀገራቱ ተወካዮች በአሁናዊ ዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያላቸውን እይታ ለተሳታፊዎች አካፍለዋል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስትራቴጂክ እቅድና ክትትል ዋና ዳይሬክተር መኮንን ጎሳዬ÷ኢትዮጵያ አሁን ላይ በዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያላትን እይታ አስመልክተው ገለጻ አድርገዋል፡፡

መድረኩ የብሪክስ አባል ሀገራት በውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው ላይ ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን መለዋወጥ እንደሚያስችላቸው መገለጹን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.