Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና አልጄሪያ በማዳበሪያ ዘርፍ በትብብር ለመስራት መከሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ከአልጄሪያ የኢነርጂ፣ ማዕድንና ታዳሽ ኃይል ሚኒስትር መሐመድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በአፈር ማዳበሪያ ምርት ዘርፍ በትብብር ሊሰሩባቸው በሚችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፍ እና ሥርጭት እንዲሁም ከሀገራቱ የጋራ ፍላጎት እና ትብብር የሚጣጣሙ መስኮችን መለየት ላይ መወያየታቸውም ተገልጿል፡፡

በውይይቱ ኢትዮጵያ እየተገበረች ያለው የኢኮኖሚ ሪፎርም ለኢንቨስትመንት ይበልጥ ምቹ ከባቢን መፍጠሩ ተጠቅሷል፡፡

ኢትዮጵያ ዘለዓቂ ልማትና የጋራ የኢኮኖሚ ለውጥን በሚደግፍ መልኩ ከአልጄሪያ ጋር ያላትን አጋርነት ለማጠናከር እንደምትሻ መግለጿን የተቋሙ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.