የጋምቤላ ክልል ም/ቤት መደበኛ ጉባዔ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ የ18 ካቢኔ አባላትን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቅቋል።
የካቢኔ አባላት ሹመቱ የጸደቀው ቀደም ሲል በሹመት ላይ ሆነው በጉባዔው ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ያልፈፀሙ እና የቦታ ሽግሽግ ያደረጉ ናቸው ተብሏል።
በዚህ መሰረትም:-
1. አቶ ማበር ኮር——— የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ ፓል ቱት———የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
3. ወ/ሮ ክርምስ ሌሮ———የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
4. አቶ ኡኩኝ ኡኬሎ———የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ
5. ዶክተር አቤል አሠፋ ——— የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ
6. አቶ ኡጁሉ ኡዶል———የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ
7. አቶ ሯች ባየክ———የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
8. ኡማን አሙሉ (ዶ/ር)——— የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ
9. አቶ ቸንኮት ዴቪድ——— የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
10. ዴቪድ ሯች (ዶ/ር)——— የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ
11. ወ/ሮ ኛሞች ጊል———የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ
12. አቶ ላክዴር ላክባክ——— የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
13. አቶ ኮንግ ኩላንግ———የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ቢሮ ኃላፊ
14. ወ/ሮ አሪያት ኡጁሉ———የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
15. አቶ አምቢሳ ያደታ———የክልሉ አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ
16. አቶ ዶል ኡኩሪ ———የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ
17. ወ/ሮ ባንቻየሁ ድንገታ———የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ
18. አቶ ጀሙስ ኞች———የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሾመዋል።
በተጨማሪም አቶ ቱት ቶትን የክልሉ ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡