በወልቂጤ ከተማ የኢፍጣር መርሐ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡
በመርሐ ግብሩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እና በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች መታደማቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡