የኢትዮጵያና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንን ትብብር የሚያጠናክር ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በኢትዮጵያና በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡