Fana: At a Speed of Life!

የጉራጌ ጀፎረ የገጠር ኮሪደር አሁን ላለው የምህንድስና ጥበብ አብነት ነው – ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጉራጌ ጀፎረ የገጠር ኮሪደር አሁን ላለው የምህንድስና ጥበብ አብነት ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተናገሩ።

ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የገጠር ኮሪደር አካል የሆነውን መንጠር ቀበሌ ይሰፋአጣጥ መንደር ‘ጀፎረ’ን በጎበኙበት ወቅት፤ የመንገድም ሆነ ሌሎች የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ሲካሄድ የወሰን ማስከበር ጉዳይ ተግዳሮት ነው ብለዋል።

የጉራጌ ማህበረሰብ ባለው ሀገር በቀል ጥበብ ሰፋፊ የገጠር ኮሪደር ልማት ጠብቆ ማቆየቱን ጠቅሰው፤ የመሬትን ወሰን በባህላዊ የዳኝነት ጥበብ ጠብቀው በማቆየት ምቹ፣ ጽዱና ውብ አካባቢ ለትውልድ ላስረከቡት የጉራጌ አባቶች ምስጋና አቅርበዋል።

ጀፎረ የገጠር ኮሪደር ልማት በሀገር በቀል እጽዋት የደመቀና ጽዱ አካባቢ መፍጠር እንዳስቻለ መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

“ጀፎረ” ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት የሚከናወንበት የጉራጌ ባህላዊ መንደር ሲሆን÷ የጉራጌ ማህበረሰብ ከጥንት ጀምሮ ያዳበረው የአኗኗር እሴት ጥበብ ነፀብራቅ መሆኑ ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.