ሴፕ ብላተር እና ሚሼል ፕላቲኒ ከቀረበባቸው ክስ በድጋሚ በነፃ ተሰናበቱ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞ የፊፋ ፕሬዚዳንት ሴፕ ብላተር እና የቀድሞ የዩኤፋ ፕሬዚዳንት ሚሼል ፕላቲኒ ከቀረበባቸው በፊፋ የፋይናንሺያል የስነ ምግባር ጥሰት ክስ በነፃ መሰናበታቸው ተገልጿል።
ሁለቱ የቀድሞ የእግር ኳስ ከፍተኛ ኃላፊዎች በፈረንጆቹ 2011 ላይ ፈፅመዋል ከተባሉበት የ2 ሚሊየን ዶላር ማጭበርበር ወንጀል ክስ በስዊዘርላንድ ፍርድ ቤት በድጋሚ ነፃ መውጣታቸውን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡
በፈረንጆቹ 2011 ከ2 ሚሊየን ዶላር በላይ የፊፋ ገንዘብ በማጭበርበር፣ በመልካም አስተዳደር እና ያለአግባብ በመበዝበዝ የተከሰሱት የ89 ዓመቱ ብላተር እና የ69 ዓመቱ ፕላቲኒ በቀረበባቸው ክስ ላለፉት ዓመታት ጥፋተኛ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ውድቅ አድርገዋል።
ብላተር ከፈረንጆቹ 1998 እስከ 2002 በፕሬዚዳንት አማካሪነት ለሚሰሩና ውል ለሌላቸው 2 ሚሊየን የስዊስ ፍራንክ፤ ፊፋ ለፕላቲኒ እንዲከፍል በፈረንጆቹ 2011 ላይ ማፅደቃቸው ቢዘገብም ለሁለተኛ ጂዜ በነፃ ተሰናብተዋል።