በቻይና ናንጂንግ የተሳተፈው ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አቀባበል ተደረገለት
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና ናንጂንግ በተካሄደው 20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብቷል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጀግና አቀባበል የተደረገላቸው መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ መረጃ አመላክቷል።
ለልዑካኑ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ መኪዩ መሃመድ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች አቀባበል አድርጎላቸዋል።
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው 2 የወርቅ እና 3 የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም 3ኛ እንዲሁም ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን ማጠናቀቋ ይታወቃል፡፡