Fana: At a Speed of Life!

‎ኢትዮጵያ ድንቅ ሕዝብ አላት – የምሥራቅ አፍሪካ ጥበባትና ባህል ፌስቲቫል ተሳታፊዎች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ባስተናገደችው ሁለተኛው የምሥራቅ አፍሪካ ጥበባትና ባህል ፌስቲቫል ላይ ለተሳተፉ የቀጣናው ሀገራት ባህልና ጥበባት ሚኒስትሮችና ልዑክ ሽኝት ተደረገ፡፡

በሚኒስትር ዴዔታ ማዕረግ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አማካሪዎችን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለእንግዶቹ አሸኛኘት አድርገዋል፡፡

እንግዶቹም ኢትዮጵያ ላሳየቻቸውን የእንግዳ አቀባበል ሥርዓት ምሥጋና ማቅረባቸውን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

“ኢትዮጵያ ድንቅ ሕዝብ ያላት ሀገር ናት፤ በቆይታችንም ትልቅ ማስታወሻ ሆናችሁናል” ሲሉም እንግዶች ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.