Fana: At a Speed of Life!

አገልግሎቱ  ከባለድርሻ አካላት  ጋር  የኢፍጣር  መርሐ- ግብር  አካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከባለድርሻ አካላት ጋር የኢፍጣር መርሐ- ግብር አካሄደ፡፡

በመርሐ-ግብሩ ላይ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም  ተጋባዥ እንግዶች፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡

የኢፍጣር መርሐ-ግብር  በተቋም ደረጃ  መከናወኑ፤  በመረጃና ደኅንነት የሥራ  ዘርፍ ውስጥ ያሉ  የሀገር  ውስጥና የውጭ ባለድርሻ አካላትን አብሮ የመሥራት ባህል፣ ወዳጅነትንና ትብብርን ይበልጥ እንደሚያጎለብት  ተገልጿል።

በረመዳን ወቅት ተቀራርቦ በማፍጠር፣ መጠያየቅና ፍቅርን ማሳየት የጾሙ ልዩ መገለጫ መሆኑን   አገልግሎቱ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የላከው መረጃ አመላክቷል፡፡

በኢፍጣር መርሐ-ግብሩ ላይ የተለያዩ የሀገር ውስጥ የፀጥታና መረጃ አካላት እንዲሁም ከአገልግሎቱ ጋር በትብብር የሚሠሩ የውጭ  ባለድርሻ አካላት  መገኘታቸውም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.