Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባለድርሻ አካላት ወጣት ፈጣሪዎችን እንዲያበረታቱ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ወጣት ፈጣሪዎች የማምረት አቅማቸውን ያሳድጉ ዘንድ የንግዱ ማሕበረሰብን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ፡፡

እራስን የመቻል እና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች በተተኪ ምርት ለመቀየር የመቻል ሀገራዊ ኅልማችን የሚሳካው ቀጣይነት ባለው ፈጠራ እና ጠንክሮ በመሥራት ብቻ ነው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በ ‘ክኅሎት ኢትዮጵያ’ ውድድር አማካኝነት ወጣቶች ችሎታቸውን እና ሐሳባቸውን ወደ ትርጉም ያላቸው ተግባራዊ ፈጠራዎች ለውጠው እየተገበሩ በማየቴ ደስተኛ ነኝ ሲሉም በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በፈጠራ ሥራ ላይ የተሰማሩት ወጣቶችን ያበረታቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሌሎች ወጣቶችም የማሕበረሰባችንን አንገብጋቢ ፍላጎቶች እንዲመረምሩ እና ሀገራቸውን ለማገልገል የሚችሉ መፍትሔዎችን እንዲፈጥሩ አበረታታለሁ ብለዋል፡፡

የንግዱ ማሕበረሰብን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እነዚህን እና ሌሎች ወጣት ፈጣሪዎች የማምረት አቅማቸውን ያሳድጉ ዘንድ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.