Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኦርዲን ረመዳንን በመደጋገፍ ማሳለፍ እንደሚገባ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁን የረመዳን ወር እርስበርስ በመደጋገፍ በጎ ተግባራትን በማከናወን ማሳለፍ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

አቶ ኦርዲን ታላቁን የረመዳን ወር በማስመልከት በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች ማማዕድ አጋርተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም፤ ታላቁን የረመዳን ወር እርስበርስ በመደጋገፍ በጎ ተግባራትን በመፈጸም ማሳለፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በጾሙ እርስበርስ የመደጋገፍን ዕሴትን በይበልጥ ማጎልበት ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በተለይም ምዕመናኑ በዚህ የጾም ወቅት በየአካባቢያቸው የሚገኙ አቅመ ደካማ ወገኖችን በመጎብኘት እና ያለው ለሌለው በማካፈል እንዲያሳልፍ ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.