ከኢንዱስትሪዎች የሚወጣ ፈሳሽ ቆሻሻን ለመቆጣጠር የሚያስችል ዲጂታል ሥርዓት ሥራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዳማ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ከኢንዱስትሪዎች የሚወጣ ፈሳሽ ቆሻሻን በዘመናዊ መንገድ ለመቆጣጠር የሚያስችል ዲጂታል ሥርዓት ሥራ አስጀምሯል፡፡
የዲጂታል ሥርዓቱ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍ እንደሚያግዝ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
በአዳማ የተጀመረውን ልምድ በመውሰድ በሌሎች የኢኮኖሚ ዞኖች ላይ ለመተግበር ይሠራል ማለታቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡