Fana: At a Speed of Life!

ከቱርክ በመጡ የሀኪሞች ቡድን በቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 3 የኩላሊት ንቅለ ተከላ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከቱርክ ሀገር የመጡ የሀኪሞች ቡድን በቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት ሦስት የኩላሊት ንቅለ ተከላን በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የህክምና ባለሙያዎቹ ቡድን በቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት ላደረጉት የኩላሊት ንቅለ ተከላ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር በርክ ባራን የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ ማዕከል በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ለማቋቋም የሚያስችል ፕሮጀክት ላይ ከዶክተር መቅደስ ዳባ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.