በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፍጻሜ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሚካሄደው 20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፍጻሜ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ።
በሴቶች 800 ሜትር ቀን 9 ሰዓት ከ54 የአምናው የርቀቱ አሸናፊ ጽጌ ዱጉማ እና ንግስት ጌታቸው ለአሸናፊነት የሚጠበቁ አትሌቶች ናቸው።
ከቀኑ 9 ሰዓት ከ28 ላይ በሴቶች የ1500 ሜትር ፍጻሜ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ እና አትሌት ድርቤ ወልተጂ ይወዳደራሉ።
ኢትዮጵያ እስከ አሁን በሻምፒዮናው በአትሌት ፍሬወይኒ ኃይሌ በ3000 ሜትር ሴቶች ወርቅ እና በወንዶች 3000 ሜትር በአትሌት በሪሁ አረጋዊ የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።
ኢትዮጵያ ሁለት ሜዳሊያዎችን በማግኘት በሜዳሊያ ሰንጠረዡ አራተኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ፥ አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና ኩባ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።