Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እንሰራለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጥራት ያለው እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሳፈሩት ጽሑፍ ÷ በከተማ አስተዳደሩ ለወረዳ አመራሮቻችን ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና መጠናቀቁን አስፍረዋል፡፡

ስልጠናው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የተጀመረውን  መሠረታዊ ለውጥና የሪፎርም ሥራ ይበልጥ ውጤት እንዲያስገኝና ብቃት ያለው የሕዝብ አገልጋይ ለመፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ  ያለባትን ሃላፊነት ለመወጣትና ለነዋሪዎች ቀልጣፋና የላቀ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ብቁና የአገልጋይነት መንፈስ የተላበሰ አመራር በመገንባት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የአመራር ምልመላና ስምሪት በብቃትና በክህሎት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን በማድረግ ለነዋሪዎች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.