Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና እንግሊዝ በጤና ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዝ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የጤና ደህንነት ላይ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በእንግሊዝ የአፍሪካ ግሎባል ጤና ቡድን መሪ ዶ/ር ኡዞአማካ ጊልፒን እና ሌሎች የጤና ዘርፍ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በጤና ሥርዓት፣ በወረርሽኝ ምላሽ እና በሰው ሃብት ልማት የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ዶ/ር መቅደስ በኢትዮጵያ ለወደፊት የጤና ድንገተኛ አደጋዎች የተሻለ ምላሽ ለመስጠት፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋንን ለማስመዝገብና የጤና ሽርዓቱን ለማጠናከር የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከእንግሊዝ ጋር ያላት አጋርነት በጤና ደኅንነት ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ፣ የማይበገር የጤና ሥርዓትን ለመገንባትና ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ዶክተር ኡዞአማካ ጊልፒን በበኩላቸው÷ኢትዮጵያ በጤና ሥርዓት ማሻሻያ ሒደት እያስመዘገበች ያለውን እድገት አድንቀዋል፡፡

እንግሊዝ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የጤና ደህንነት ላይ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቀርጠኛ ናት ማለታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.