Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ የፖሊስ ኮሚሽነሮች መደበኛ ጉበዔ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌደራል፣ የክልል እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ የፖሊስ ኮሚሽነሮች መደበኛ ጉበዔ ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ወቅት የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግሥቴ በሪፎሙ በወንጀል መከላከልም ሆነ በወንጀል ምርመራ ብቁ ሆኖ ለመገኘት እንደተቋም ትልልቅ ሥራዎችን ስንሰራ ቆይተን አስደናቂ ውጤቶችን አስመዝግበናል ብለዋል።

አክለውም ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እና የሰብዓዊ መብት አያያዝን በማጠናከር ሀገራዊ ራዕይን ለማሳከት ሁሉም መረባረብ እንዳለበት ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሕገ-መንግሥቱንና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን እንዲሁም ሌሎች ሕጎችን በማክበርና በማስከበር ሕብረተሰቡን በወንጀል መከላከልና ምርመራ በማሳተፍ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት እየጠበቀ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በጉባዔው ማንኛውም የወንጀል ተጠርጣሪ የትኛውም ክልል ተደብቆ ማምለጥ በማይችልበት ሁኔታ ላይ መወያየት እንደሚገባም ማሳሰባቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል።

ሀገሪቱ የጀመረችው የኢኮኖሚ ሪፎርም ግቡን እንዲመታ የፀጥታ ዘርፉ አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በወንጀል መከላከልም ሆነ በወንጀል ምርመራ ከዚህም በላይ አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገብ ይኖርብናል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.