ኢትዮጵያ በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና ናንጂንግ እየተካሄደ ባለው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች የ3000 ሜትር ፍጻሜ በአትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ አማካኝነት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።
ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ብርቄ ኃየሎም አምስተኛ ወጥታለች።
ከቀኑ 8 ሰዓት ከ33 ላይ በሚካሄደው የ3000 ሜትር ወንዶች ፍጻሜ አትሌት በሪሁ አረጋዊ፣ አትሌት ጌትነት ዋለ እና አትሌት ቢኒያም መሐሪ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ።
በተመሳሳይ አትሌት በሪሁ በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል፡፡
አትሌት ቢኒያም መሐሪ 9ኛ እና አትሌት ጌትነት ዋለ 11ኛ በመውጣት ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል።
ኖርዌያዊው አትሌት ጃኮብ ኢንብሪግስተን ርቀቱን በቀዳሚነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆኗል።