የኢትዮ- ቱርክ የጋራ የኢኮኖሚና ንግድ ትብብር ኮሚሽን የዝግጅት ስብሰባ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 9ኛው የኢትዮ- ቱርክ የጋራ የኢኮኖሚ፣ ንግድና የቴክኒክ ትብብር ኮሚሽን የዝግጅት ስብሰባ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ ያስሚን ወሀብረቢ÷ስብሰባው ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር ያላትን የኢኮኖሚ ግንኙነት ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየት ያለመ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራት ንግድ ለማሳደግና የኢትዮጵያን ንግድ ሚዛን ጉድለት በማጥበብ ረገድ በትብብር መስራት እንደሚያስችል ነው ያስረዱት፡፡
በስብሰባው ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተወከሉ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች መሳተፋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡