Fana: At a Speed of Life!

ውጊያን በመሳሪያ ቴክኖሎጂና በውሰን የሰው ኃይል የመጨረስ አቅም ተገንብቷል – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አየር ኃይል፣ ሳይበርና ሜካናይዝድን በማዘመን ውጊያን በመሳሪያ ቴክኖሎጂ እና በውስን የሰው ኃይል የመጨረስ አቅም ተገንብቷል ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።

የሜካናይዝድ ዕዝ ያሰለጠናቸውን የሜካናይዝድ ሙያተኞች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በዚህ ወቅት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንደገለጹት÷የመከላከያ ሠራዊቱን አቅም በክህሎት እና ዘመኑ ባፈራቸው ትጥቆች በራስ አቅም ማዘመን ተችሏል።

ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት የገጠሟትን ፈተናዎች ሁሉ በድል የተወጣችው በጀግኖች ልጆቿ መስዋዕትነት እንደሆነ መግለጻቸውንም የመከላከያ ሠራዊት መረጃ አመላክቷል።

ይህ የአሸናፊነት ሥነ-ልቦና ዛሬም በእያንዳንዱ ወታደር ልቦና ውስጥ መኖሩን ነው ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ያወሱት፡፡

ከተመረቁ የሜካናይዝድ ሙያተኞች የታየው ወጤትም ጠላቶች ደጋግመው እንዲያስቡ የሚያደርግና ጦርነትን በሩቁ ለማስቀረት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

ተቋሙን ያደራጀነውም አሁናዊ የዓለም የጦርነት ባህሪን ግምት ውሰጥ በማስገባት ነው ብለዋል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.