Fana: At a Speed of Life!

በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በሰመራ ከተማ የተገነባው የዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ያስገነባው የዳቦ ፋብሪካ ተመርቋል።

የዳቦ ፋብሪካው ከዚህ ቀደም እንደተገነቡት የዳቦና ዱቄት ፋብሪካዎች ተመሳሳይ አቅም እንዳለው ተገልጿል።

ፋብሪካው 420 ኩንታል ስንዴ በቀን መፍጨት የሚችል ሲሆን÷ 300 ሺህ ዳቦዎችንም በ24 ሰዓታት ማምረት እንደሚችል የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

የዳቦ ፋብሪካው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ታሳቢ በማድረግ በየክልሉ ከተገነቡት 14 ዳቦና ዱቄት ፋብሪካዎች አንዱ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ፋብሪካውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በተገኙበት ነው የተመረቀው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.