Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የአፋር ክልል የግብርና እና የኢንዱስትሪ አቅሞችን የሚያሳዩ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በአፋር የግብርና እና የኢንዱስትሪ አቅሞች የሚያሳዩ ቁልፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

ጉብኝታቸው ከስድስት ወራት በፊት ምርት የጀመረውንና 15 ቶን በሰዓት የሚያመርተውን የአዮዳይዝድ ጨው ማምረቻ ምልከታን ያካተተ እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

በተጨማሪም በአፋር ክልል የተሳካ የበጋ ስንዴ ምርት እየተካሄደበት ያለውን ልማት ሥራ እና የአይሮላፍ መኖ ባንክ ልማት ማዕከልን ተመልክተዋል።

በክልሉ ስላለው የግብርና አቅም የነበረውን የተሳሳተ ምልከታ በማሸነፍ በመስኖ የለማ አስደናቂ የስንዴ ምርት መገኘት እንደተቻለም የጽሕፈት ቤቱ መረጃ አመላክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ቀዳማዊት እመቤቷ በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነባውን እና ከማሳ ወደ ገበታ ሙሉ የምግብ ምርት ሰንሰለት የሚያጎላውን ዘመናዊ የዳቦ ፋብሪካም መርቀዋል።

ፋብሪካው በተገጠሙለት ዘመናዊ ማሽኖች በመጠቀም 420 ኩንታል ስንዴ በቀን መፍጨት የሚችል ሲሆን÷ 300 ሺህ ዳቦዎችንም በ24 ሰዓታት ማምረት ይችላል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.