Fana: At a Speed of Life!

ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ዘርፍ ያለው ትብብር ተጠናክሮ ይቀጥላል – ፊንላንድ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፊንላንድ ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ዘርፍ ያላትን የተለያዩ ትብብሮች ማጠናከር እንደምትፈልግ ገለፀች፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና የላቲን አሜሪካ ጉዳዮች ኃላፊ አምባሳደር ሄሌና አይራክሲነን ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ በትምህርት ዘርፍ የቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተከናወኑ ያሉ ዋና ዋና ተግባራትን በተመለከተ ለልዑካን ቡድኑ አብራርተዋል።

ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትን ለሁሉም ዜጎች በሁሉም አካባቢ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ከአጋር አካላት የሚደረጉ ድጋፎች ያለምንም የሀብት መባከን ህፃናት እና ታዳጊዎች ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ በሚያስችሉ ተግባራት ላይ ለማዋል በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አምባሳደር ሄሌና አይራክሲነን በበኩላቸው÷በትምህርቱ ዘርፍ ፊንላንድ ከኢትዮጵያ ጋር በርካታ ተግባራትን በትብርብር ማከናወኗን ጠቅሰዋል።

ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፃቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.