Fana: At a Speed of Life!

የምሥራቅ አፍሪካ የባህል እና ኪነ-ጥበብ ፌስቲቫል ሕዝቦችን አሰባሳቢ ነው- ሚኒስትር ገርቫስ አባዬሆ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ የባህል እና የኪነ-ጥበብ ፌስቲቫል ማኅበራዊ ትብብርን የሚያበረታታ መሆኑን የቡሩንዲ የምሥራቅ አፍሪካ ማሕበረሰብ ጉዳዮች፣ ወጣቶች ስፖርት እና ባህል ሚኒስትር ገርቫስ አባዬሆ ገለጹ፡፡

በተጨማሪም ፌስቲቫሉ፤ የባህል ልውውጥ፣ ዲፕሎማሲ እና የኢንዱስትሪ እድገትን እንደሚያበረታታ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ የባህል ውዝዋዜዎች ከኢትዮጵያ ውዝዋዜዎች ጋር በብዙ መልኩ ተመሳሳይነት እንዳላቸው ሚኒስትሩ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም የቡሩንዲ ውዝዋዜ እና ጥበብ እንደ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ታንዛኒያ ካሉ ጎረቤት ሀገራት ጋር ይመሳሰላሉ ብለዋል፡፡

ትናንት በአዲስ አበባ መካሄድ የጀመረው ሁለተኛው የምሥራቅ አፍሪካ የባህል እና ኪነጥበብ ፌስቲቫል እስከ መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች ይቀጥላል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.